በሐዋሳ በፓርኪንግ የተሰማሩ ማኅበራት ተገቢውን ገቢ ማግኘት አልቻልንም አሉ

‹‹የፓርኪንግ ታሪፍ በ30 ደቂቃ እስከ አራት ብር መሆኑ የተጋነነ ነው›› አሽከርካሪዎች

በአስፋው ብርሃኑ፣ ልዩ ዘጋቢ ከሐዋሳ

በሐዋሳ ከተማ በፓርኪንግ ሥራ የተሰማሩ አዳዲስ ማኅበራት አሽከርካሪዎች ስለማይተባበሩን ገቢያችንን በአግባቡ መሰብሰብ አልቻልንም ሲሉ፣ አሽከርካሪዎች በበኩላቸው በ30 ደቂቃ እስከ አራት ብር የተወሰነው ታሪፍ የተጋነነ እንደሆነ ገለጹ፡፡