ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን ፍላጎት ያልው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ለዘጠና ሰከንድ ማስታወቂያ 100,000 የአሜሪካን ዶላር ለመቀበል ተስማማ

ኢትዮ እማማ
የዓለማችን የረዥም እርቀት ባለክብረወሰን የሆነው ብርቅየው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ከታዋቂው መጠጥ ከጆኒ ዎከር ጋር የማስታወቂያ ሥራ ለመስራት ተፈራረመ።ይህም የመጀመሪያው አፍሪካዊ ያደርገዋል።

አትሌቱ ባለፈው ሐሙስ በሸራተን አዲስ በላሊበላ አዳራሽ የስኮትላንድ ውስኪ ከሆነው ከታዋቂው መጠጥ ከጆኒ ዎከር ካምፓኒ ጋር ባደረገው የአንድ አመት ስምምነት ለዘጠና ሰከንድ በቴሌቪዥን ለሚተላለፈው ማስታወቂያ 100,000 የአሜሪካን ዶላር ይከፈለዋል።ማስታወቂያው በአፍሪካ፣በላቲን አሜሪካና በአውሮፓ ይተላለፋል።

“አትሌቱ በኢትዮጵያ ለበርካታ ወጣት አትሌቶች እንደሞዴል የሚታይ በመሆኑ ለገንዘብ ብሎ የአልኮል መጠጥ የሆነውን የጆኒ ዎከር ውስኪን እየቀመሰ ማስታወቂያ መስራቱ ፤ወጣቱ ትውልድ ወደመጠጡ እንዲገፋፋ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር ያውም እሱን ከመሰለ አንድ ታዋቂ አትሌት የሚጠበቅ አይደለም” የሚሉ በርካቶች ናቸው።አትሌቱ ግን ይህንን አባባል አይቀበለውም።”ሕዝቡ ይሚጠጣ ከሆነ የእኔ አላፊነት አይደለም፤አላፊነቱን የሚወስደው የጠጣው አካል ነው “በማለት መልሷል።

በሌላ በኩል አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ልምምዱን እያደረገ ሲሆን ከስፖርት ዓለም ሲገለል ወደ ፖለቲካው ዓልም እንደሚገባ ዛሬ ከሮይተርስ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ይፋ አድርጓል።”ለኢትዮጵያ አንድ ነገር ማድረግ እፈልጋለው ፤ለአፍሪካ፣ለእራሴም፣ለቤተሰቤና ለሕዝቤ” የሚለው አትሌት ኃይሌ በፖልቲካ ውስጥ በመሳተፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይንም ፕሬዝዳንት አሊያም ሚኒስቴር የማይሆንበት ምክንያት እንደሌለ ገልጾ አሁን ግን ከውዲሁ ይህ እንደማያሳስብውና ምክንያቱም የሚያስባቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉት ይናገራል።ለሎንደኑ 2012 ኦሎምፒክ እየተዘጋጀ እንደሆነ የሚገልፀው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ከሁለት ሳምንት በፊት ልምምዱን እንደጀመረና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጾ በመጪው የካቲት ወር በጃፓን ቶክዮ በሚካሄደው
ውድድር አቋሙን እንደሚፈትሽና ጥሩ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ከወዲሁ ገልጿል።