በጋምቤላ ክልል የወያኔ ወታደሮች ሶስት ሰዎች ገድለው ሁለት አቆሰሉ

በጋምቤላ ክልል ፉኚዶ ከተማ የመከላከያ ማዘዣ ጣቢያ ውስጥ በድንገት በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት መቁሰላቸው ተሰማ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡት የአካባቢው ምንጮቻችን እንዳስታወቁት በድንገት አካባቢውን አሸብሮ የነበረው ተኩስ መነሻው ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች ወታደራዊ የማዘዣ ጣቢያ ውስጥ ዘልቀው ገብተዋል በሚል ስጋት ነው።

ጥር 19 ቀን 2004 ዓ ም ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ገደማ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ መታየታቸውን ተከትሎ በያቅጣጫው መተኮስ የጀመሩት በጋምቤላ እየተስፋፋ ያለውን የመሬት ነጠቃ የሚቃወሙትን ለመቆጣጠር በክልሉ የተሰማሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው።

ምንጭ http://www.solidaritymovement.org