የኢትዮጵያ ህዝብ፣ … ከዚኽ ወዴት? (ክ.14 አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አራት
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
በዚኽም መሠረት ምንም እንኳን ድርጅቶች በተናጠል የሚያደርጉት ትግል በተባበረና በተቀናጀ መልክ መሆን ይችል ዘንድ የጋራ ብሔራዊ ግንባር (ትብብር) እንዲመሠረቱ በብዙ ቅን-አሣቢ፣ ዴሞክራትና አገር-ወዳድ ወገኖች በኩል ሙከራዎች ያልተቋረጡ ቢሆንም በተለይ ኢአጉ ከተመሠረተበት ከሰማንያ ዘጠኝ ዓ.ም. ጀምሮ ድርጅቶች የትግል ግንባር እንዲፈጥሩ የእንቅስቃሴው ዋና ነጥብ (አጀንዳ) አድርጎ መያዙና ያላሰለሰ ጥረት የእንቅስቃሴአቸው አካል አድርገው ማየትን አላቆሙም።