መፍትሄው አንድ ብቻ ነው! (አንዷለም አራጌ)
በዚህ በሠለጠነው ዘመን በኢኮኖሚ፣ በፍትሕና በዴሞክራሲ ከፍተኛ እመርታ በአስመዘገቡ አያሌ የዓለማችን አገሮች መሀከል በርካታ የአፍሪካ አገሮች ሕዝብ በጥቂት አፄዎች የጭቆና ቀንበር ሥር እየማቀቀ ይገኛል፡፡ ጭቆናው በጥቂቶቹ ላይ ደግሞ እጅግ የከፋ ነው። ከጥቂት እጅግ የከፋ አፈና ከተንሰራፋባቸው አገሮች መካከል ደግሞ ግንባር ቀደሟ አዛውንቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነች።