በጋዜጠኞቹ ላይ የተላለፈውን የቅጣት ውሳኔ ጠበቆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ተቃወሙ

“ይግባኝ እንጠይቃለን” ተከላካይ ጠበቆች

ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይልና በሽብርተኝነት ድርጊት ለማናጋትና ለማፈራረስ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል በሚል ክስ ተመሥርቶባቸው በነበሩት ኤልያስ ክፍሌ፣ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ሒሩት ክፍሌና መምህርትና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም. የተላለፈውን የቅጣት ውሳኔ ጠበቆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው መቃወማቸውን አስታወቁ፡፡