የ"ፀረ-ሙስና" ቀን Anti-Corruption Day
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ ኅዳር 30 (December 9) ቀን በዓለም ደረጃ የሙስና አስከፊነት የሚዘከርበት ("ፀረ-ሙስና") ዓመታዊ ቀን ነው። የችግሩ አስከፊነት በተለይም በታዳጊ አገሮች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈጥር ከመሆኑ አንጻር ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተገቢ ነው። "ደጀ ሰላም" ማንሣት የፈለገችው ግን በጠቅላላው በኢትዮጵያ ስላለው ሙስና እና የንብረት ብክነት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችንን ጠፍንጎ ስለያዛት ዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ነው። ከላይ እስከ ታች በተዘረጋ የጉቦ፣ የሙስና እና የሀብት ዝርፊያ ዘመቻ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ መውደቋን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችንን በማስታወስ መፍትሔው ግን አሁንም ሩቅ መሆኑን አበክረን እናስታውሳለን።(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
