አንድነት ፓርቲ እሁድ ጥር 24 በደሴ ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ ያካሂዳል

አንድነት ፓርቲ እሁድ ጥር 24 ደሴ የሚያካሄደው ሰልፍ ከከተማው አስተዳዳር እውቅና የተሰጠ ሲሆን ሰልፉ በደሴ አራዳ አከባቢ ከሚገኘው የአንድነት ቢሮ ተነስቶ መጨረሻ ሆጤ አደባባይ ነው የሚያበቃው። ሰልፉ ከ2:00 እስከ 7:00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን እንደተለመደው የደሴና የአከባቢዋ ህዝብ በነቂስ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ አንድነት በቀጣይ እሁድ በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በደብረታቦር እና በሌሎች የክልል ከተሞች ላይ ሰልፍ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ነው የሚገኘው።