የበረዶ ዉሽንፍር በአሜሪካ

የዩናይትድ ስቴትስን ሰሜን ምሥራቃዊ ግዛቶች ጠንካራ የበረዶ ዉሽንፍር እንደመታ ዘገባዎች ያመለክታሉ። እስከ60 ሴንቲ ሜትር እንደሚደርስ የተነገረዉ እጥጥ ባዘቶ ብናኝ ወርዶ የሚከመረዉ በረዶ በተለይ የኒዮርክ ግዛትን ከነፋስ ጋ ተዳምሮ ነዉ የገረፈዉ።