ግቡን የሳተ ቀስት!
ነጻው ፕሬስ – አዲሱ የ’ኢሕአፓ’ ጠላት!?
ከአትክልት እና ጓደኞቹ
የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ላለፉት 20 ዓመታት በእሳት የተፈተኑ ቁርጠኞች ናቸው። እስርና እንግልቱን በተደጋጋሚ የወጡበት የወረዱበት ሸክም ነው። በጠራራ ፀሀይ በወያኔ ጥይት የተገደሉትን መርሳት ይከብዳል። ህክምና ተነፍገው ዘብጥያ ውስጥ የሞቱትንም ማስታወስ እንዲሁ… ይሰቀጥጣል። ዛሬም ወፍራም ወፍራም ክስ ተለጥፎባቸው ቃሊቲ ውስጥ የሚጉላሉትንም ልብ ይሏል።