ምርኮኛ – ቅኝት መስፍን ማሞ ተሰማ (ሊያነቡት የሚገባ)

የመጸሐፉ ደራሲ ቆንጅት ብርሃን

መንደርደሪያ

ደምና ዕንባ ተቀላቅሎ በብዕር ሲቀሰም ምንን ይወልዳል? ምርኮኛ! ምርኮኛ የደም መፅሀፍ ነው።  የዕንባ መፅሀፍ። የአንድ ትውልድ ደም፤ የአንድ ትውልድ ዕንባ የተተረከበት የደም ዕንባ ታሪክ። ምርኮኛ አንባቢን ምርኮኛው አድርጎ በትርክቱ ባህር እየደፈቀ፤ ትንፋሽ እስኪያጥር ነፍስ እስክትቃትት አካልና መንፈስን ረግጦ የሚገዛ፤ ሃያል የደም ዕንባ ታሪክ ነው – ያልታደለው ትውልድ ታሪክ።