የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ማሠልጠኛ ሜዳና የመዝናኛ ማዕከሉ ይዞታ ሆስፒታል ሊገነባበት ነው
(በውድነህ ዘነበ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊዝ ቦርድ ከቦሌ መድኃኒዓለም ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ በኩል የሚገኘውን የቀድሞ ቀበሌ 23 መዝናኛ ማዕከልና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማሠልጠኛ ሜዳን ጨምሮ፣ 24,000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ቦታ የአሜሪካ ኩባንያ ለሆነው ለአፍሪካ-አሜሪካ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሆስፒታል መገንቢያ እንዲሰጥ ወሰነ፡፡