የአምስት ዓመቱ ዕቅድ ከቁጠባ ብዙ ይጠብቃል
– ቁጠባው ጡረታን፣ መኖሪያ ቤትንና የቦንድ ሽያጭን ያካትታል
(በውድነህ ዘነበና በአስራት ሥዩም)
ከትናንት በስቲያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተቀማጭ ገንዘብ ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ወለልን ከአራት ወደ አምስት በመቶ ከፍ ያደረገ ሲሆን፣ ዕርምጃው የቁጠባ ባህልን ለማበረታታትና ጥቅም ላይ ያልዋለ ሙአለ ነዋይን ለመጠቀም መሆኑን ገልጿል፡፡