የአዲስ አበባ አስተዳደር አዲስ የንግድ አሠራር ለውጥ ሊያፀድቅ ነው

–    የነዳጅ ማደያዎችን የልኬት መሣርያዎች ትክክለኛነት መፈተሽ ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ተሰብስቦ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የሚያቀርብለትን አዲስ የንግድ አሠራር የለውጥ (ሪፎርም) ፕሮግራም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡