የማንነት ጥያቄ ያነሱ የሸካሽ ጎሳ ማኅበረሰብ በረሃብ አደጋ ላይ ነን አሉ

– ወደ አጎራባች ክልል የተፈናቀሉት ቁጥር ወደ 80 ሺሕ ይጠጋል

በሶማሌ ክልል መንግሥትና በፀጥታ ኃይሎች ደረሰብን ባሉት የኃይል ጥቃት ሳቢያ ወደ አጎራባች ክልል (ኦሮሚያ) ተፈናቅለው የሚገኙት የዱቤና የሸካሽ ጎሳ ማኅበረሰብ፣ ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን በተወካዮቻቸው አማካይነት ለሪፖርተር ገለጹ፡፡