አስተዳደሩ በመሀል ከተማ 660 ሔክታር መሬት ለማልማት አዲስ ዕቅድ አወጣ

•    ከቦታው ላይ የሚነሱ ነዋሪዎችን ማወያየት ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመልሶ ልማት ፕሮጀክቶቹን በማስፋት፣ በቀጣይነት በመሀል ከተማ በሚገኙ ዘጠኝ ቦታዎች ላይ የሰፈሩ ነዋሪዎችን በማንሳት 660 ሔክታር መሬት ለመልሶ ልማት እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡