የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት የሶማሌን ባለስልጣናትን ማሰራቸው ተገለጸ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2004 ዓ.ም. January 18, 2011)፦ ሁለቱ ባለስልጣናት የታሰሩት እሁድ ከሰዓት የሰላም ስምምነቱን ካፈረሱ በሁዋላ መሆኑን ሶማልላንድ ፕሬስ ዘግቡዋል። የታሰሩት ባለስልጣናት አደን አብድላሂ አወል የሱማሌ ክልል አኩ ሱና ፓርላማ ቡድን መሪ እና አብዱልፈታህ ሀሰን ጃማ የሸበሌ ቫሊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት መሆናቸው ታውቋል