ከግንቦት 7 ፍርደኞች የአቶ አሳምነው ጽጌ ባለቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተማፅኖ ደብዳቤ ጸፉ
(በታምሩ ጽጌ)
በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም. በህቡዕ በመሰባሰብ መንግሥትን በኃይል ለመጣል በመስማማትና ግንቦት 7 ከሚባለው አሸባሪ ቡድን ጋር በመቀላቀል ተሳትፈዋል በሚል አምስት ክስ ተመስርቶባቸው በሁሉም ጥፋተኛ ተብለው በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው መካከል፣ የአቶ አሳምነው ጽጌ ባለቤት ቤታቸው እንዳይወረስባቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተማፅኖ ደብዳቤ ጻፉ፡፡