ወሎ ዩኒቨርስቲ ጠፋ የተባለው ተማሪ ልብሱ በደም ተበክሎ ተገኘ
(ፍኖት) — ደሴ ከተማ በሚገኘው ወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአስደንጋጭ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ የዜና ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ እንደዜና ምንጮቻችን ገለፃ:: ‹‹በዩንቨርሲቲ ውስጥ ከሚማሩ ተማሪዎች ውስጥ ከአንድ ሳምንት ጀምሮ የተወሰኑ ተማሪዎች ባልታወቀ ሁኔታ ተሰወሩ ተብሎ ሲነገር ከረመ፡፡ ጠፉ ከተባሉት ውስጥ አንዱ ከምስራቅ ጎጃም ዳንግላ ወረዳ ሊሳ ቀበሌ የመጣው ተማሪ ሀብታሙ መለሰ አንዱ ነው፡፡
ዩኒቨርስቲውም መጥፋቱን ለማሳወቅ ፎቶ ግራፉን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለጥፎት ነበር፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ጠፋ የተባለው ተማሪ ጠፋ በተባለበት ዕለት የለበሰው ልብሱ በደም ተበክሎ ተገኘ፡፡
በዚህም የተነሳ ተማሪዎች ተረብሸው በመሰብሰብ ዩኒቨርስቲው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡ ምንም መልስ ባለማግኘታቸው የዞኑን ሀላፊዎች በሰልፍ ለመጠየቅ ግቢውን ለቀው ሲወጡ አድማ በታኝ ፌደራል ፖሊስ ደብድቦ ወደ ግቢ መለሳቸው፡፡
በአሁኑ ግዜ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚወጣም ሆነ የሚገባ ተማሪ የለም፡፡ ተማሪዎች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ››በማለት ገልፀዋል፡፡ ወደ ህትመት እስከገባንት ሰዐት ድረስ የአካባው ፖሊስ ሀሳብ እንዲሰጥበት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡
በአንድነት ፓርቲ የምትታተመዉን የፍኖት ጋዜጣን፣ በብዛት ለማተም፣ በስፋት ለማሰራጨትና ሕዝቡን ለማንቃትና ለማደራጀት ገንዘብ ያስፈልጋል። ገዢዉ ፓርቲ የመንግስትን አዉታራት ብቻዉን ተቆጣጥሮ፣ ከሕዝብ ካዝና እየወሰደ ፣ ለሕዝብ ጥቅም ከዉጭ አገር የተገኙን እርዳታዎችን ወደ እራሱ እያዞረ ለመንቀሳቀስ ይሞክራል። የአንድነት ፓርቲ የሚተማመነዉ በሕዝብ ድጋፍ ብቻ ነዉ። ለሰላምና ለዲሞክራሲ፣ ለኢትዮጵያ አንድነትና ለዜጎች እኩልነት የሚደረገዉን ትግል ይቀላቀሉ።በገንዘብዎት ትግሉን ይርዱ።