አቡጊዳ – የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት ተከፈለ -የአላሙዲ ሰዎች አንደኛዉን ተቆጣጥረዉታል
ለበርካታ አመታት ኢትዮጵያዉያንን ሲያሰባሰብ የነበረዉ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዉያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት ተክፈለ።
ከሼክ አላሙዲ ጋር ግንኙነት ባላቸዉ ጥቂት ግለሰቦች ችግር ላይ የወደቀዉ ይህ ፌዴሬሽን፣ ያለፈዉ አመት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በክብር እንግድነት በመጋበዙ ዙሪያ በዉስጡ በተፈጠረዉ አለመግባባት፣ ትልግ ዉዝግብ ዉስጥ ገብቶ እንደነበረ ይታወቃል። በከፍተኛ የሕዝብ ግፊት ወ/.ት ብርቱካን አትላንታ በተደረገዉ የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ ንግግር እንዳደረጉም የሚታወስ ነዉ።
ያኔ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እንዳይጋበዙ ሲኦሰሩ የነበሩ፣ እንደ አቶ ዳዊት አጎናፍር ያሉ ግለሰቦች፣ በፌዴሬሽኑ እንቅስቃሴ ላይ አሁንም ትልቅ ችግርና ጫና እየፈጠሩ በመሆኑ፣ በርካታ የቦርድ አባላትን ያቀፈ አዲስ ፌዴሬሽን መቋቋሙንም የደረሰን ዜና ያመለክታል።
« ESFNAOne Bringing Ethiopians Together» በሚል ስም የተቋቋመዉ ይህ አዲስ ፌዴሬሽን ፣ በስሙ አዲስ ይሁን እንጂ የቀድሞ ፌዴሬሽን ዉስጥ የሚሰሩ አብዛኞችን ያቀፈ ሲሆን በበርካታ ቡድኖችም ዘንድ ድጋፍ ያለዉ ፌዴሬሽን እንደሆነ ይነገራል።
ፌዴሬሽን በሕግ የተመዘገበ ሲሆን ከቅዳሜ ጁላይ 11 እስከ ጁላይ 7 2012 ባሉት ቀናት በዋሺንገትን ዲስ የኢትዮጵያዉያንን እግር ኳስ ዉድድሮች እንደሚያከናዉን የፌዴሬሽኑን መግለጫ በመጠቀስ የደረሰን ዘገባ አክሎ ያትታል።
ፌዴሬሽኑ ዲሴምበር 29፣ በሰሜን አሜሪካ ላሉ ቡድኖች በጻፈዉ ደብዳቤ ፣ በሎስ አንጀለስ ጃኑአርይ 13 ቀን 2010 በሚደረገዉ ስብሰባ ቡድኖች ተወካዮች እንዲልኩ፣ የሆቴልን የመጓጓቻ ወጭ ፌዴሬሽኑ እንደሚሸፍንም ገልጿል።