የፍኖት ጋዜጣ – አቶ አቤል ሰይፉ በግል ድርጅቶች ጡረታ አከፋፈል ዙሪያ ለፍኖት የሰጡት አስተያየት

ጥቆማዬም መንግስት አዲስ የጡረታ አዋጅ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም የተነሣ የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በግል ድርጅቶች ውስጥ 15,16 አመት የሰሩ ሰራተኞች አሉ፡፡ በድርጅቱ በኩል የአገልግሎት እየተቆረጠ ሲጠራቀምላቸው ነበር፡፡ ገንዘቡም በርካታ ነው፡፡ የተማረ የሰው ሀይል ያለባቸው ድርጅቶች ለምሳሌ፡- የግል ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች ወዘተ የመሳሰሉት ሰራተኞችን በመወያየት ሰራተኛው ይሄ ገንዘብ ይመለስልን በማለቱ ገንዘቡ ተመልሶላቸዋል፡፡

የተማረ የሰው ሀይል የሌላባቸው የጥበቃ አስጠባቂ ኤጀንሲዎች የኮንስትራክሽን ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎች ወዘተ. . . ሰራተኛውንም አላወያዩም፤ ገንዘቡንም አልመለሱም፤ በደሀው ላብ በመነገድ ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ድርጅቶች ከላይ ከላይ ነቃ ነቃ ያሉ ሠዎችን በዘዴና በጥቅም በመያዝ ዝቅተኛውን ሰራተኛ ላቡን ቀምተውታል፡፡ የትም አይደርስም፤ በማለት መብቱን ረግጠዋል፤ በጥበቃ አስጠባቂ ድርጅቶች ውስጥ ከ15,000 በላይ ሰራተኞች አሉ፡፡ በኮንስትራክሽን ድርጅቶች ውስጥ በ100,000 የሚቆጠሩ የሣይት /የመስክ/ ሰራተኞች አሉ፡፡

ሠራተኛው በአሁን ሰዓት በቁጭት፣ በሀዘንና፣ በጭንቀት ላይ ነው፤ አሠሪዎችንም፣ ሰራተኞችንም፣ የሚመለከተውንም የመንግስት አካል ብታናግሩና መፍትሄ ቢበጅለት መልካም ነው እንላለን፡፡

አያውቁም አይከሱም ተብሎ የድሆችን ገንዘብ መቀማት ተገቢ አይደለም፡፡ በዚህ ላይ ዘገባ ብትሰሩበት ሰራተኛውም እንዲያነበው ነው፡፡ በጥበቃ አስጠባቂ ድርጅቶች ላይና በኮንስትራክሽን ድርጅቶች በፋብሪካዎች ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ ትኩረት ቢደረግባቸው፡፡ እያልኩ ሀሳቤን አጠቃልላለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር አቤል ሰይፉ

የአንድነት ፓርቲ ተግባራዊ እንቅስቃሴ፣ ሆደ ሰፊነትና ታጋሽነትንም ጭምር የሚያሳይ እንቅስቃሴ በመሆኑ ምስጋና ሊወረወርላቸው ይገባል እላለሁ፡፡

የፍኖት ነጻነት ጋዜጣ በተሳምንቱ በአንድነት ለዲሞርካሲና ለፍትህ ፓርቲ የምትታተም ጋዜጣ ናት። ጋዜጣው በብዛት እንዲታተም ፣ በስፋት በየክልሎቹ እንዲሰራጭ እርዳታዎትን የአንድነት ፓርቲ ይጠይቃል።

የፍኖት ጋዜጣ እትም 24ን በሙሉ ለማንበብ ክለዚህ ይጫኑ !