በወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ረብሻ 2 ተማሪዎች ሞቱ

(አቡጊዳ) — ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞተው ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ አንድ የውስጥ አዋቂ እደሚሉት ከሆነ ደግሞ “ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው” ይላሉ፡፡

የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ሲራጅና ከማል የተባሉ ሁለቱ የሕግ ተማሪዎች መሞታቸውንና ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው
የተፈፀመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው በተደጋጋሚ ደውለን ይመለከታቸዋል የተባሉትን ኃላፊዎች ለማነጋገር ጥረት ብናደርግም ስልካቸው ስለማይነሳ የተጣራ መረጃ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ሆኖም ግን አንድ ስሜ እንዲጠቀስ አልፈልግም ያሉ ግለሰብ እንዳሉት “በእርግጥ ልጆቹ ሞተዋል፡፡ የሞቱት ግን በግጭት ሳይሆን “በምግብ መመረዝ ነው” በማለት ግጭቱን አስተባብለዋል፡፡
ምንጭ