የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሠራተኞች ምደባ እያወዛገበ ነው

– ለቦርድ ሰብሳቢውና ለውኃ ሀብት ሚኒስቴር ደብዳቤ ጽፈዋል

(በታምሩ ጽጌ)

 

የኢትዮጵያ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በቅርቡ በልዩ ሁኔታ በዋና ሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ የተመደቡት ሠራተኞች የምዘና መስፈርት ሕገወጥ መሆኑን አንዳንድ ሠራተኞች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡