የመደበኛ ስልክ ጥሪዎች ቅናሽ ተደረገ
• የከተማ ታሪፍ የሚስተካከለው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው
ኢትዮ ቴሌኮም በመደበኛ የስልክ መስመር ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ለሚደረጉ ጥሪዎች በአንድ ደቂቃ ያስከፍል የነበረውን ዋጋ በ55 እና በ80 ሳንቲም ሲቀንስ፣ የከተማ ውስጥ የመደበኛ ጥሪዎችን ዋጋ ግን ማስተካከል የሚቻለው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ብቻ እንደሆነ ተገለጸ፡፡