አቡጊዳ – የኢትዮጵያ ጦር የሶማሊያን ስትራቴጂክ ከተማ፣ በለትወኔን ተቆጣጠረ
የኢትዮጵያ ወታደሮች በሂራን አዉራጃ የምትገኘዋን በለትወኔ የምትባለዉን ስትራቴጂክ ከተማ እንደተቆጣጠሩ ቢቢሲ ዘገበ።
ኢጋድ የተሰኘዉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ስብሰብ፣ የሶማሊያ የጎሮቤት አገሮች ለአፍሪካ ሕብረት ጦር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ኬንያ በደቡብ በኩል አልሻባብ ላይ ጥቃቷን ስታጠናክር ፣ ኢትዮጵያም በደቡብ ምእራብ በኩል ልትንቀሳቀስ እንደምትችልም ብዙዎች ይጠብቁ ነበር።
በደቡብ በኩል በኬንያ ፣ በሰሜን በኩል በቡሩንዲ ጅቡቲና ኡጋንዳ ጦር እየተገፋ የመጣዉ የአልሻባብ ቡድን፣ በምእራብ የተነሳበት የኢትዮጵያ ጦር፣ በሶስት ማእዘን እንዲከበብ ያደረገዉ ሲሆን ፣ በተለይም ይደግፈዉ በነበረ በኤርትራ መንግስት ላይ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታዉ ምክር ቤት፣ ጠንካራ አቋም መዉሰዱ፣ የፈረንሳይና የአሜሪካ ኔቪዎሽ በደቡብ ሶማሊያ ድንበር የሕንድ ዉቂያስን በቅርበት የሚቃኙ መሆናቸው፣ በደቡብ ሶማሊያ በተነሳዉ ረሃብ ሕዝቡ እርዳታ እንዲያገኝ አልሻባብ ካለመተባበሩ የተነሳና ቡድኑ በሚያራምደዉ ጭካኔ የተሞላበት የሸሪያ ሕግ ምክንያት በሕዝብ ዘንድ ያለዉ ተቀባይነት ማሽቆልቆሉ ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ ፣ ቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ ከሁሉም ማእዘናት ከከፈቱበት ዉጊያ ጋር ተደምሮ የአልሻባብን እድሜዉ እያሳጠረዉ መምጣቱትን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
የሶማሊያ 2/3 ግዛት የሚሆኑት የሶማሌላንድና የፑትላንድ ግዛቶች፣ እራሳቸዉን ችለዉ ፣ በሕዝብ የተመረጡ መንግስታት መስርተዉ ፣ ጸጥታን አስጠበቀዉ የሚኑሩ ሲሆን ፣ በተቀረዉ 1/3 በሚሆነዉ በደቡን የሚገኘዉ የሶማሊያ ግዛት ሰላም የሚመጣበትን ዘመን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶማሌዎች በጉጉት የሚጠበቁት እንደሆነ ይታወቃል።
ዋን ከተማዋ ሃርጌሳ የሆነዉ በኢሳቅ ጎሳዎች የተሞላችዉ ሶማሌላንድ፣ ከሶማሊያ ተገንጥላ ለብቻዋ አገር መሆን የምትፈልግ ሲሆን፣ ዋና ከተማዋ ጋራዌ የሆንችዋ ፑትላንድ በፌደራል አወቃቀር በአንዲት ሶማሊያ ዉስጥ መቀጠል የምትፈልግ ናት።