የሆስተሷን ዓይኖች ባጠፋው ፍርደኛ ላይ የተሰጠው ቅጣት ተቃውሞ አስነሳ
‹‹ውሳኔው ጥሩ ነው ወይም አይደለም ለማለት ከደንበኛችን ጋር አልተወያየንም›› የተከሳሽ ጠበቆች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የበረራ አስተናጋጅ (ሆስተስ) የነበረችውን አበራሽ ኃይላይን ዓይኖች ማጥፋቱ በተረጋገጠበት የቀድሞ ባለቤቷ አቶ ፍስሐ ታደሰ ላይ ታኅሣሥ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የተወሰነው የ14 ዓመታት ፅኑ የእስራት ቅጣት ተቃውሞ አስነሳ፡፡