እሳት ማቀጠሉን እንዲያውቁ አዲስ አባበን አቃጥለን አናሳይ ነገር። በዳዊት ዳባ
የጥፋት ሀይል ነው፤ ይህ ቡድን ጭራሽ ለሀዝብ ከበሬታና ፍቅር የለውም፤ አገር ሻጭ ነው፤ በጭራሽ የሚታመን አይደለም፤ ጨፍጫፊ ነው። በአጠቃላይ ከሴጣን ነው የምትጋቡ፤ በርምጃችሁ አናንተም ወገኖቻችሁንም ትጎድበታላችሁ። የመለስን መንግስት በሚመለከት እነዚህን በመሰሉ ጉዳዬች ላይ ለያንዳንዳቸው ይዘቱ ቅዱሱን መፀሀፍ የሚያካክል መረጃዎች ሊቀርብበት የሚችል ፍፁም የሆነ እውነትነት ያላቸው ክሶች ናቸው የሚነሱት። ጊዜው ሲመጣ በሀገር ክህደት፤ በዘር ማጣፍት በመሳሰሉ ክብደት ባላቸው ወንጀሎች አስከሳሽ ናቸው። አዲስ ህግ ማርቀቅ ሳያስፈልግ ባወጡት ህግ የመለስ መንግስትም ድርጅታቸውም ወንጀለኛ ይሆናል። ከወንጀለኛ ጋር በምንም ሁኔታ ማበር ወንጀለኛነት ነው። በኛ አገር ሁኔታ ከወያኔ ጋር መሞዳመድ ፍፁም ከሀዲነትም ነው። አስላ ሾሽት አመት ያልሞላው ካልሆነ ይህን የወያኔ ባህሪና የሚያመጣውን ጣጣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በደንብ ማወቅ ነበረበት ያውቃልም። እፉ ነው ተብለው ተደጋግሞ ቢነገራቸውም እጃቸውን ሰደው ተቃጥለው ካላዩ የማይሰሙ የህፃን ባህሪ ያላቸው ዜጎች ግን ሁሌም አሉን።
ወያኔ በህዳሴው ግድብ ለማጭበርበርና ገንዘብ ለመቃረም ሞክሮ ሚኒያፖሊስ፤ አትላንታ የመሳሰሉ ብዙ ከተሞች አፍንጫህን ላስ ተብሎ ተመልሷል። ትንሽም ቢሆን መቃረም የቻለው እኛ ከተማ ነው። የመረጃ ችግር የለም ዳኮታ አይደለም ዳላስ ነው። ለዛውም የነቡሽ አገር… we are the Cowboys መሆናችን ነው። በነገራችን ላይ ጥሬ ገንዘብ እየሰጠን የቦንድ ወረቀት እንዲሰጡን የተመደቡልን መሪዎቻችን በደንብ የሚታወቁ ቀንደኛ የትግራይ ወያኔዎች፤ ቤተክርስትያን ከፋፋዮችና በፍርድ ቤት ተሟጓቾች ናቸው። በእርግጥ ተሳታፊዎች ከጠቅላላው የዳላስ ነዋሪ በጣም ጥቂቶች ናቸው ። ከወያኔ ጠቅላላ በህሪ አኳያ በምንም መንገድ ጠቂቶችም ከዚህ ቡድን ጋር መጎዳኘት ነበረባቸው ወይ?። መልሱ ቀላል ነው በጭራሽ።
በኛ ሰርጎ ገቦች ሙሉው የገንዘብ መቃረሚያ ስብሰባቸው ተቀድቶ ነበር። አነሳሳችን ሰምተነው የሚስብ ሆኖ ስላገኘነው ስብሰባው ላይ ትንሽ ለማለት ነው። ተናጋሪ እንግዶች አንባሳደር ውቤና ብሩ ግርማ ናቸው። ታሪካቸው ሲቃወሙ ሲቃወሙ ሞቱ ወይ መሸጥና መግደሉን ማን ፈቅዶላቸው በአጫፋሪነት ሲያገዳድሉ ሲያሻሽጡ ፤ ለዚህም ጠርቀም ያለ ሲከፈለቻው ሲበሉ ሲበሉ ሞቱ ከሚሉት ሁለት ምርጫዎች ከብዙዎቹ የወያኔ ሰዎች በተለየ አንባሳደሮቹ ማወዳደርና ማሰብ የሚችሉ መሆናቸውን ያሳዩበት ስብሰባ ነበር። ለጊዜው ሁለተኛውን ትክክል ሆኖ ታይቷቸዋል። ያም ሆኖ እንግዶች ሚዛናዊ፤ ምሁራዊ ሊሆን ብዙ ጥረዋል። በየትኛውም መንገድ ይሁን ፍፁም የሆነ ጥረታቸው በመለስ ዘንድ ሞገስ ይሆን ዘንድ ላንባሳደሮቹ አጥብቀን እንፀልያለን። በስብሰባው ካነሷቸው ጉዳዮች።
– ምን አልባት ላልሰሙና ቦንድ ገዝተው ለመክበር ለተገኙ ዜጎች የህዳሴው ግድብ የሚገነባው ቦርደር ላይ ስለሆነና ቦታው ላይ ለእርሻ የሚሆን መሬት ስለሌ ይህ ሁሉ የሀገር ሀብት ፈሶበት ይሰራል የተባለው ግድብ ኤሌክትሪክ ሀይል ከማመንጨት ወጪ ልንጠቀምበት አንችልም። ምን አልባት አሳ ልናረባበት ወይ ታንኳ ልናንሸራሽርበት እንችል ይሆናል ነው የተባለው። በብዙ አቅጣጫ ለምን የሚለውን ጥያቄ ለሚያስነሱ ጉዳዮች ማብራርያ ሆን ተብሎ ታልፏል። ለሱዳን መሬት ባንሰጥስ ኖር ብሎ የጠየቀም ተሰብሳቢም የለም።
– ለንቆቅልሽነት በሚመስል ቦንድ ገዥዎች መልስ እንዲሰጡ የአባይን ግድብ ተግባራዊ ለማድረግ ለሀገር ጥቅም ጠበቃ ለመሆንና መሰዋትነት ለመክፈል የሚችል መንግስት አስፈላጊነት ተወስቷል። አቀራረቡ ታሪክን የማመሳአከርን አስፈላጊነትን ጠቋሚ ነበር።
– ቦንድ መግዛት ለመንግስት ማበደር ማለት ነው። “አባባሉ ቦንድ ስትገዙ ለመለስ አበደራችሁ ማለት ነው በቀጥታ ይሆናል”። ተጋባዥ እንግዶቹ በምሳሌ ሲያስረዷቸውም ተመሳሳይነት ባይኖረውም ሀይለስላሴ ከውጪ የተበደሩትን መንግስቱ ከፍሏል። መንግስቱ የተበደረውን ያሁኑ እየከፈለ ነው። በተመሳሳይ ለመለስ ያበደረችሁትን ገንዘብ ቀጥሎ የሚመጣው መንግስት እንደሚከፍላቸው ለቦንድ ገዥዎች ተነግሯቸዋል። ቦንድ ገዥዎችም አጨብጭበዋል።
– ቦንድ ከገዛችሁ መለስ ቀረጡን ያልፋችሗል ተብለዋል። የሚገዙት ግን በሌላ አግር ገንዘብ መሆኑ ተለይቶ እንደሚመዘገብ ተግልፆላቸዋል። አገሮቹ ገንዘባቸው ሌላ አገር ላይ ለመዋለ ንዋይ ሲውል ምን ያህል እንደሚቀርጡና እዚህ ጉዳይ ላይ የያገሩን ህግ እንዲመረምሩ ጥያቄ አጫሪ ነበር።ቦንድ ገዝቶ ሀብታም ለመሆን ላልቸኮለ ማለት ነው። ለየሚኖሩበት አገር የሚቀርጡት ለመዋለ ንዋይ ላፈሰሱት የሚከፈላቸው ወለድ ወይ ክፍያቸው ተቀናንሶ አትራፊነቱ ተከድኖ ይብሰል ተብሎ ታልፏል።
– አንተ እያለህ እንዴት እንራብ አንጠማ ብለን በዘፈኑም በግጥሙም አባይ ላይ እንቆጭ ነበር አይነት አባባሎች አንባሳደሮቹ በስብሰባው ላይ አውስተዋል። ይህ ግድብ እንጀራና ንጹህ የመጠጥ ውሀ እንዴት እንደሚሆነን ግን ግልጽ አልተደረገም። ነገር ግን አባይን ስንገድብ አንድ ጠብታ ውሀ ሳይቀንስ ለግብፆች እንዲደርሳቸው ከፍተኛ ጥናትና ትኩረት እንደተደረገበት ደግሞ ለቦንድ ገዥዎች ተነግሯቸዋል።
ታዳሚዎች ቦንድ ገዝተው። አባይ ተገድቦ። ከዛም ህብታም ሆነው ብቻ ነው የሚታያቸው የሚመስሉት። በጠቅላላው ያለፈውንና አሁን ወያኔ የሚጠፋውን ወንጀል በሙሉ ወሾን ያነሳ ወሾ ነው በሚለው ብልህ በማጣፋት በህዳሴው ግድብ ብቻ ወያኔን ማየት የታደሉ ወገኖቻችን ስብሰባ ነበር።ስብሰባው ላይ እንደተለመደው በመሬት ቅርምቱ ላይ ምንም የተፈናቀለ ዜጋ የለም የመሳሰሉ ሽምጥጥ አድርጎ መካድ አይነት ብዙ ውሸቶች ነበሩበት። በቼክ ቦንድ መግዛት እንችላለን? የመሳሰሉ የደደብ ጥያቄዎችም ተስተናግደዋል።
ውቤ ከረሜላ
December 30, 2011