ከሳሞራ የኑስ ጋር የማይስማሙ ጄነራሎች ተባረሩ !
አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል።
ለአቶ መለስ ዜናዊ በጣም ታማኝ የነበሩትና በቅርቡ ግን ከጄነራል ሳሞራ የኑስ ጋር ለመስማማት ችግር የነበራቸዉ ጄነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልን ጨምሮ በርካታ መኮንኖች እንዲሰናበቱ የተደረገ ሲሆን፣ በቅርቡ የሌተና ጀነራልነት ማእርግ የተሰጣቸዉም እውቁ የኦሮሞ ጀነራል፣ ባጫ ደበሌም ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።
መኮንኖችን በዚህ ሁኔታ የማሰናበቱ ሂደት፣ የመከላካያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባንጸባረቀ መልኩ እንዲዋቀር ለማድረግ የታሰብ ሳይሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንድ ቤተሰብን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቆም እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። “ጦሩን ለማሻሻል፣ አሁን ያሉትን በአዳዲስ ኦፊሰሮችን ለመተካት ታስቦ ከሆነ፣ እነ ሳሞራ የኑስ መልቀቅ ነበረባቸዉ” ያሉን ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ በጦር ኃይሉ ዉስጥ ሊነሳ የሚችልን ተቃዉሞ ለማፈን ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት እንደሆነ ይናገራሉ።
በተለይም በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት በተለየ ሁኔታ፣ የትግራይ ሕዝብ ለሰላምና ለዲሞክራሲ የሚደረገዉን ትግል መቀላቀሉ፣ ገዢዉ ፓርቲ በዘጠና ሰባት የትግራይ ተወላጆችን ከሌላዉ ሕዝብ ለማጣላትና ለማራራቅ የተጠቀመበትን የዘር ካርድ መጫወት እንዳልቻለ የገለጹት እኝሁ ተንታኝ “የትግራይ ተወላጆች በብዛት በመኮንንነት ያሉበት የጦር ኃይል ፣ እንደ ዘጠና ሰባቱ ከሳሞራና ከመለስ ጎን ተሰልፎ በሕዝቡ ላይ የተመኮስ አዝማሚያዉ በጣም የወረደ ነዉ። በመሆኑም በጦሩ ላይ ብዙ እምነት ስሌላቸዉ ነዉ እያደረጉ ያሉትን የሚያደርጉት” ሲሉም አስየያየታቸዉን አክሎእዉ ሰጥቷል።
በምርጫ 2002 ወቅት አረጋዊ ገብረ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ የመድረክ አባላትን ደጋፊዎች መገደላቸዉና መታሰራቸዉ ይታወቃል። በቅርቡም በመቀሌ አካባቢ በሺሆች የሚቆጠሩ የትግራይ ነዋሪዎች በግፍ ከቤታቸው እንዲባረሩ በሰፊ ተዝግቧል።