ፍትህ ጋዜጣ በጫና እና በማስፈራሪያ የሚዝሉ ክንዶች፤ የሚሰደዱ እግሮች የሏትም!

አሁን አደገኛ ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ፍትህን ወደ መቃብር ለመክተት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የሚሴረው ሴራ እና የሚሸረበው ተንኮል ስጋና ደም ለብሶ እነሆ ከበር ቆሟል። ከረቡዕ (11/04/2004) ጀምሮ በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ፤ እንዲሁም በአዘጋጆቹ ሙሉነህ አያሌው እና ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ ላይ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ክትትል እየተደረገ ሲሆን፣ ይሄ ርዕሰ አንቀጽ እየተዘጋጀም (13/04/2004) የጋዜጣው ቢሮ በክትትል ቀለበት ውስጥ እንደሆነ ነው።