አሸባሪነትን” ማን ያገኛታል… ስለ ህዝቡ በፅናት የታገለ አይደለምን?
አቤ ቶኪቻው
ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ? ሁሉ ሰላም ሁሉ መልካም ይሆን ዘንድ አጥብቄ እመኝልዎታለሁ። “አጥብቆ የተመኘ ከሰጠ እኩል ነው” የሚለውን አባባልም እመርቅልዎታለሁ። አንተስ እንዴት ነህ? ካሉኝ፤ የእኔ ነገር እንግዲህ ገና ሚናው ያለየለት ስደተኛ አይደለሁ? አንዴም ሲጨንቀኝ፣ አንዴም ሲጨምቀኝ ብቻ አለሁ እንደምንም፤ እግዜር የሰጠውን ሰው አልችል አይልም! እልዎታለሁ።