የሸራተኑ ምሽት – በአቶ በረከት መጽሐፍ

የሁለት ምርጫዎች ወግ Yehulet Mirchawoch Wogአዲስ አድማስ ጋዜጣ

– አቶ በረከትና ሼኽ መሐመድ አሊ አልአሙዲ የተደናነቁበት ምሽት

– አቶ መለስ፣ ኢሕአዴግና አልአሙዲ ተወድሰዋል

– ኢሕአዴግ “የሕዝብ ፍቅር ያለው ፓርቲ” ተብሏል

– በመጽሐፉ ተቃዋሚዎች ክፉኛ ተተችተዋል – በተለይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

የኢሕአዴግ ነባር ታጋይ፣ የቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር፤ አሁን ደግሞ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም በምርጫ 97 ጉልህ ስፍራ የነበራቸው አቶ በረከት ስምኦን ጻፉት የተባለውን መጽሐፍ ለማንበብ በጉጉት ስጠባበቅ ነበር። ባለፈው ማክሰኞ በመጽሐፉ ምረቃ ላይ ለመታደም ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ያመራሁትም ከዚህ ጉጉት በመነጨ ስሜት ነው።