በረከት ስምኦን በመጽሐፋቸው ስለማን ምን አሉ?

ባለፈው ማክሰኞ በሸራተን አዲስ የተመረቀው የአቶ በረከት ስምኦን ‹‹የሁለት ምርጫዎች ወግ›› እንደተጠበቀው ተቃዋሚዎችን የሚያብጠለጥል፣ እንደተገመተውም ኢሕአዴግን የሚያንቆለጳጵሱ ታሪኮችን ይዞ ቀርቧል፡፡