አቡጊዳ – «ሳንፈቅድላቸዉ ፤ ሃያ አመታቸው» በታላቁ ሩጫ ህዝቡ ከተናገረዉ

በአዲስ አበባ በተደረገዉ ታላቁ ሩጫ እንደ ወትሮው ሕዝቡ በሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ላይ ያለዉን ብሶት ምሬት ገለጸ።

በሩጫዉ የተሳተፉ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ወጣቶች በተቀናጀና በተቀነባበረ መልኩ የተለያዩ ዜማዎችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን፣ አቶ መለስ ዜናዊ የሙአመር ጋዳፊ እድል እንደሚገጥማቸዉ በመግልጽ ለእኝሁ አምባገነን መሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ጋዳፊ የተመኩበት ሰራዊታቸዉና የደህንነት አባሎቻቸዉ በጥቅምና በገንዘብ የገዟቸዉ ባሪያዎቻ ከሕዝብ ቁጣ ሊጠብቋቸዉ እንዳልቻሉ፣ በስተመጨረሻም ተዋርደዉ እንደሞቱ ይታወሳል።

«ሳንፈቅድላቸው ፣ ሃያ አመታቸዉ» እያሉ በከፍተኛ ድምጽ ሲያዜሙ የተሰሙት ወጣት ኢትዮጵያዉያን ሯጮች፣ ገዢዉ ፓርቲ ለሃያ አመታት የገዛዉ የሕዝብ አመኔታንና ፍቃድ አግኘቶ ሳይሆን በጉልበትና በጠመንጃ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል።

በሯጮቹ የተንጸባረቀዉ ታላቅ ተቋዉሞ ፣ የገዢው ፓርቲ አባላትና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ከሆኑት እጅግ በጣም ጥቂቶች በስተቀር፣ ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ የሚሆነዉ ህዝባችን የሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ እንዳንገፈገፈዉ ፣ የሚያመላክትና ማስተዋል፤ ከፈለጉ ለዘመኑ ባለስልጣናት ትልቅ የማስጠንቀቂያ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ ብዙዎች ይናግራሉ።

የኑሮ ዉድነት ፣ በአገዛዙ ካድሬዎች በየጊዜዉ የሚደርሱ ዜጎችን የማዋረድ፣ የመዝለፍና ክብራቸዉን የመንካት ድርጊቶች፣ በየቦታዉ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተንሰራፉት ጉቦኝነትና ሙስና፣ ከአቅም በላይ መሆኑን የገለጹት ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ሕዝቡ ባልታሰበና ባልተጠበቀ ሁኔታ መሮት ሊነሳ እንደሚችል፣ የተነሳም እለት፣ ከአቶ መለስ ጀምሮ እያንዳንዱ አሁን የአፈና የግፍ ተባባሪ የሆኑ ሁሉ ሊያመልጡ እንደማይችሉ በማስጠንቀቅ ፣ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣናት ፀሐይ ሳትጠልቅ፣ ለራስቸዉ ሲሉ ለአገር የሚበጁ እርምጃዎች እንዲወስዱ፣ መሰረት በሌለው በሽብር ክስ የሚያስሯቸዉን ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈቱና ለብሄራዊ እርቅ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

በታላቁ ሩጫ የነበረዉን ሁኔታ በአጭሩ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ