የሰሞኑ ሹክሹክታ – የቅዳሜ ማስታወሻ (Tesfaye Gebreab)

ከድሬዳዋ ተነስተው ኤርትራ ቀይ ባህር ዳርቻያረፉት የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተሮች ጉዳይ ለወያኔ ራስ ምታት ሆኖበት ሰንብቶአል። ሄሊኮፕተር ይዘው ኤርትራ የገቡት ኢትዮጵያውያን የአየር ሃይል አብራሪዎች ማንነት እና በወያኔ ላይ ያላቸው ተቃውሞ ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም። በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከማንኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሽባ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። አማራ እና ኦሮሞ የጦር አይሮፕላን አብራሪዎች ከስራ ውጭ ተደርገዋል። የትግራይ አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች ደ’ሞ በጣት የሚቆጠሩ በመሆናቸው አየር ሃይልን በትግራይ ሰዎች ብቻ ለማንቀሳቀስ አልተቻለም። በተለይም ክኒሻኖች በአብዛኛው አማራና ኦሮሞዎች በመሆናቸው ወያኔ ችግር ውስጥ ወድቆአል። የፌክ ፌደራሊዝም ውጤት ይኸው ነው።

ከቀጣዩ ምርጫ ጋር በተያያዘ ወያኔ ብዙ ፈተናዎች ከፊቱ ተደቅነውበታል። ህወሃትና ብአዴን የስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ሰሙነኛ ወግ ነበር። ኦህዴድ ከጨዋታ ውጭ ሆኖአል። ድቡብ ህዝቦች፤ አልነበሩም – የሉምም። ኦህዴድን ያልያዘ የኢህአዴግንሊቀመንበርነት (ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ጭምር) መያዝ እንደማይችል ግልፅ ነው።ስለዚህ ህወሃትና ብአዴን የኦህዴድ አባላትን በግለሰብ ደረጃ በመቀራመት የራሳቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሻኮቱ ይዘዋል። ኦህዴድ ለራሱ እንዳያስብ ተደርጎ ስለተሽመደመደ ከፊቱ የተደቀነው ጥያቄ፣ “ማንን ላንግስ?” የሚለው ብቻሆኖአል። ርግጥ ነው፤ የኦህዴድ አባላትን በቅርብ እንደማውቃቸው አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ህወሃት ስልጣን ላይ ቢቆይ ይመርጣሉ። ግን ደግሞ በዚህ ወቅት የአካባቢያችን ዋነኛ ጠላት ወያኔ እንጂ የአማራ ፖቲከኞች እንዳልሆኑ የሚያጡት አይመስለኝም። ወያኔ ቢወድቅ ደመራው ወዴት እንደሚወድቅ አለመታወቁ ለማናቸውም ቢሆን አሳሳቢ ነው። ሁኔታዎች ተወሳስበዋል።የኦህዴድ አመራር መግባባት ችሎ ቢደራጅ ህወሃትና ብአዴንላይ ተፅእኖ ማድረግ ይቻለው ነበር። ለአብነት ከኢህአዴግ አባል ድርጅትነት ቢወጡ ጠንካራ ተደራዳሪ መሆን በቻሉ። ከፓርላማው ራሳቸውን ቢያገልሉ ወያኔ የኦሮሞን ህዝብ ማክበር በጀመረ ነበር። በርግጥ እንዲህ ያለ ወግ፣ “እንጀራ የለም እንጂ – ወጥ ቢኖር ኖሮ” እንዲሉ ሊሆን ይችላል።
የወያኔ አመራር አባላትም መስቀለኛ መንገድ ላይ ናቸው። አማራ ወደ ስልጣን ከሚመጣ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ እንደሚመርጡ ግልፅ ነው።የአቦይ ስብሃት ነባር አቋምይታወቃል። ሃይለማርያምና ደመቀ (አገውና ወላይታ – ፕሮቴስታንትና ሙስሊም) ወደ ስልጣን ሲመጡ፣ “የኢትዮጵያን ስልጣን ከአማራና ከኦርቶዶክስ አፅድተነዋል” ብሎ በሬድዮ ሲናገርተሰምቶአል። ለነገሩ የተሳሳተ አይመስለኝም። ኮሎኔል መንግስቱ በማፈራረስ የጀመረውን የኦርቶ – አማራ ቢሮክራሲ ወያኔ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆታል። ስለዚህ ብአዴን (አማራ ነው ከተባለ) የፈለገውን ያህል ቢፍጨረጨር የጋረዳለቲን በተመንግስት እንዲቆጣጠር ሌሎች አይፈቅዱለትም። ህወሃት ደብረፅዮንን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊያመጣ ማሰቡ ሲናፈስ የሰነበተው ወሬ ልክ አይመስለኝም። ደብረፅዮን የቴክኒክ ሰው ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማሽከርከር የሚቻለው ፖለቲከኛ አይደለም። በዚህ ወቅት ህወሃት ወደ ስልጣን ሊያመጣው የሚችለው ብቸኛ ተቀባይነት ያለው ሰው ቢኖር ቴዎድሮስ ነው። ትውልዱ ከአድዋ የሚመዘዘውን፣ አስመራ ተወልዶ ማደጉ የሚነገርለትን ቴዎድሮስ አድሃኖምን በመለስ ዜናዊ ወንበር ላይ ማስቀመጥም ቢሆን ግን ለህወሃት አስቸጋሪ ነው። ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚናከስ ጥርስ የለውም ተብሎ ይታማል። ኢትዮጵያን ለመምራት ደግሞ የሚናከስ ብቻ ሳይሆን፣ የሚቦጭቅና የሚያኝክ ጥርስ ያስፈልጋል። ህወሃት ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወደ ስልጣን ማምጣት ይመኙ ይሆናል። ቴዎድሮስ ስልጣኑን ቢይዝ ለህወሃት ጥቅም ነው። አደገኛ ጉዳትም ግን አለው። ጫጫታውን አይችሉትም። ከውስጥም ከውጭም የሚወረወርባቸውን የተቃውሞ ፕሮፓጋንዳ መሸከም ስለመቻላቸው ርግጠኛ አይደሉም። ስለዚህ ሃይለማርያምን ወይም እሱን የመሰለ ታዛዥ ሰው እየለዋወጡ፣ ከጀርባ እየተቆጣጠሩ ድምፃቸውን አጥፍተው ስልጣን ላይ መቆየቱን ይመርጡ ይሆናል።ሃይለማርያም በህወሃትና በብአዴን ተከቦ ስራውን ሲሰራ ሰንብቶአል። መከላከያ፣ ደህንነትና ውጭ ጉዳይን ማዘዝ አይችልም። መንግስትን መንግስት ሊያሰኙ የሚችሉት እነዚህ ሶስቱ ቁልፍ ቦታዎች ደግሞ በህወሃት የተያዙ ናቸው። በጌታቸው አሰፋ፣ በሳሞራ የኑስ እና በቴዎድሮስ አድሃኖም መዳፍ ስር ናቸው። ስለዚህ ሃይሌ ቴክሱ ስልጣን አልባ ሆኖ (በጌታ ፈቃድ) የታዘዘውን ሲሰራ ቆይቶአል። ያም ሆኖ ሃይለማርያም በተቀረው የአስተዳደር ቦታ የተቻለውን ያህል የደቡብ ሰዎችን ለመሰግሰግ መሞከሩ አልቀረም። ይህ ሁኔታ እንግዲህ ለረጅም ጊዜ በአማራ ተይዞ የቆየውን የማእከላዊ መንግስት የአስተደዳር ቦታዎች እያዳከመ ስለሚሄድ፣ የአዲሳባን ቢሮክራሲ የሰው ሃይል ሚዛን ስለሚያመጣጥነው ወያኔዎችም አይጠሉትም። ከዚህ ባለፈ ሃይለማርያም ሊያደርግ የሚችለው የለም። “ሃይሌ ጥርስ አብቅሎ እነ አባይ ፀሃዬን አልታዘዝም ማለት ጀምሮአል” የሚለውን ሹክሹክታ ለጊዜው ለማመን እቸገራለሁ። መጠበቅ ይሻላል።

ኦቦ ሌንጮ ለታ ለቀጣዩ ምርጫ ወደ ፊንፊኔ ያቀናል ሲባል ተሰንብቶ ነበር። እምን እንደደረሰ አልተከታተልኩትም። ሌንጮ ጠቅልሎ ቢገባ ግን ወያኔ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቀም አይመስለኝም። እንኳን ሌንጮ ገብቶ መረራ ጉዲና እንኳ እያዋዛ ፈተና ውስጥ ጨምሯቸዋል። በቀጣዩ ምርጫ በመጠኑም ቢሆን ወያኔን ሊፈታተን የሚችለው መረራ ጉዲና ነው። ስልጣን ይገለብጣል ተብሎ ባይታመንም ጥቂት የፓርላማ ወንበሮችን ያገኝ ይሆናል። ሌንጮ ተሳክቶለት ፊንፊኔ ገብቶ አስማተኛውን የኦነግ ባንዴራ ማውለብለብ ቢችል የምርጫ ሜዳውን ሞቅ ደመቅ ባደረገው። ወያኔም ቢጫ ወባ በሽታው በተቀሰቀሰበት ነበር። በነገራችን ላይ “ODF” የሚለው ምህፃረ ቃል Oromia Defence Force መስሎ ይሰማኛል።

አሜሪካኖች ህወሃትን እየደገፉ መሆኑ አይካድም። ህወሃትም ቢሆን ለአሜሪካ ብብቱን ከፍቶ ሰጥቶአቸዋል። አሜሪካኖች በህወሃት አመራር ባገኙት ጥቅም ደስተኛ ቢሆኑም፤የወያኔ ስርአት በስልጣን እንዲቆይ ይፈልጋሉ ማለት ግን አይደለም። “አናሳ ብሄረሰብ በስልጣን ላይ ሊቆይ ከሚችለው በላይ ገዝታችሁዋል። ከዚህ በላይ መሄድ አትችሉም። ችግር ሳይገጥማችሁ ቦታውን ብትለቁ ይሻላል።” ብለው ደጋግመው መክረዋቸዋል። ወያኔ የህዝብ ድጋፍ ስለሌለው አገሪቱን ገፍቶ ገፍቶ ገደል ይጨምራታል ብለው ሊሰጉ ይችላሉ። አሜሪካኖች እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉትን ከጀርባ ደጋግፈው ወደ ስልጣን ለማምጣት እንደሚፈልጉ ይታወቃል። ስለ ኦሮምያ ነፃነት የሚያስቡ ወጣቶችን ግን አሜሪካኖች በጣም ይፈሯቸዋል። “በኢትዮጵያ አንድነት” የሚያምን፣ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችል ወጣት ኦሮሞ ለማግኘት መከራቸውን ሲያዩ ሰንብተዋል ይባላል። የሚሳካላቸው አይደለም። በርግጥ በመጪው ዘመን የኦሮሞን ህዝብ በትክክል የሚወክል ሃይል ወደ ስልጣን ካልመጣ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ምእራባውያኑ አስጠንተው ደርሰውበታል። ያም ሆኖ ኦሮሞዎች ካላቸው አቅም አንድ አስረኛውን እንኳ እንዳልተጠቀሙ ይታመናል።

የአንድነት ሃይሎች የፖለቲካ አካሄድ ቀልድ ይመስለኛል። አንዳርጋቸው ፅጌ፣ “ነፃነትን የማያውቅ ነፃአውጪ” ብሎ ነበር። “አንድነትን የማያውቁ አንድነቶች” ከፕሮፓጋንዳ ባሻገር የትም መሄድ አልቻሉም። ኢትዮጵያዊነት ባለቤት አጥቶአል። ህይወቱን ቀርቶ እንቅልፉን የሚሰዋለት እያጣ ነው።ጠጋ ብሎ ላያቸው “አንድነቶች” በጎንደርና በጎጃም፤ በወሎና በመንዝ ተከፋፍለው ሲሻኮቱ ይገኛሉ። የጎንደር – ሸዋ ሽኩቻቸውን ሳይፈቱ ኦጋዴን ኢትዮጵያዊነትን እንዲዘምር ይመኛሉ። ብዙውን ጊዜ የአማራ ፖለቲከኞች፣ “ኦሮሞ ወንድሞቻችን” ማለት ያበዛሉ። በአማራ ፖለቲከኞች ዘንድ፣ “ግማሽ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ፋሽን ሆኖአል። በአንፃሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ “አማራወንድሞቻችን” የሚል አባባል ሲጠቀሙ ሰምቼ አላውቅም። አንደኛው ተለማማጭ የመሰለበት ምክንያቱ ምንድነው? ከልብ ስላልሆነ ይመስለኛል። “ወንድሞቻችን” የሚለው አባባል የለበጣ ነው።የኦሮሞን ህዝብ ስነልቦና “የቡርቃ ዝምታ” በተባለው መፅሃፌ ጥሩ አድርጌ በመግለፄ እኔ የአማራ ህዝብ ባለውለታ እንደሆንኩ ይሰማኛል። አሁንም አማራ ፖለቲከኛ ወንድሞቼን በግልፅ መምከር እፈልጋለሁ። ጊዜ እያመለጠ ነው። የአማራ ፖለቲከኞች ከሽማግሌ ኦሮሞዎች ጋር ዛሬውኑ ተግባብተው ለመስራት ካልሞከሩ በርግጥም ጊዜ እያመለጣቸው ነው። ሽማግሌዎቹ ቢያንስ በኢትዮጵያዊነት ስር ኖረዋል። ወደውም ሆነ ተገደው ለባንዴራው ዘምረዋል። አዲሱ የኦሮሞ ትውልድ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙን ባንዴራ አጥብቆ ይጠላዋል። አማርኛን ይጠየፋል። ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ማለት አይፈልግም። የአንድነት ሃይሎች ዛሬውኑ መባነን አለባቸው። ዮሃንስ መጥምቁ፣ “ከኔ በሁዋላ የሚመጣው በእሳት ያጠምቃችሁዋል!” እንዳለው እየመጣ ያለው የኦሮሚያ አዲሱ ትውልድ ከአበሻ ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር ስለመቻሉ እጠራጠራለሁ።

መልካም አዲስ አመት፤ መልካም የገና በአል ይሁንልን።
አላህ ይርዳን። አሜን!
733881_188600487993147_103123293_n

12 Comments on “የሰሞኑ ሹክሹክታ – የቅዳሜ ማስታወሻ (Tesfaye Gebreab)”

  1. ምነው እባካችሁ ይህንን መርዘኛ የሻቢያ ተላላኪ
    ተስፋዬ “ገብረ እባብ” ከኢትዮጵያውያን መድረኮች በሙሉ ብታባርሩልን? እሱ ከመጀመሪያው አንስቶ የሚሰራው ለሻቢያ ነው። ኢትዮጵያ ለሱ የጠላት ወረዳ ነች። አሁንም የሚለውን ስጨረሰና ስለነፈሰበት ጭር እንዳለች ዶሮ እያስካካ መንገዱን ሁሉ በኩስ እየበከለ ነው።

  2. this is a part of 30 years home work which is given to us from shabea Tesfaye Gebraab doesnt have any care to us.His mentality is that if we are united his country Eritria will not be able to grow thats why he tried day and night to divide us . I dont mind him he is doing what he suppose to do but know I have question for this web site owner why you posted his article please give me some reason

  3. አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት አሉ…………..መጀምሪያ አንተ ማነህ እና ነው ስለ ኢተዮጵያ ስለ ኦሮሞ ቀባጣሪ ያደረገህ??
    ምን እንደሚያሳፍረኝ እና እንደሚያስጠላኝ ታቃለህ? ልክ እንደ አንተ ተላላኪ ፣ አሽቃባጭ እና ሀፍርት-ቢስ መሆን………!!! ተላላኪ አሽቃባጭ እና ሀፍርት-ቢስ!!!

    ተላላኪ እና አሽቃባጭ ነበርክ አሁን ደግሞ እራስከን ቀይረህ ደግሞ ኦሮሞ ነኝ አልከን………ሌላ ተላላኪ እና ልላ አሽቃባጭ ለመሆን፡፡ ኦቦ ተስፋየ ኦሮሞነት ሰዎች ተሰብስበው ዳቦ እየቆረሱ የሚሰጥ ስም አይደለም፡፡ የኦሮሞን ልጆች አሳልፍህ እስወጋህ……..ኦሮሞነት የለም!! ኦሮሞነት ንጹህ እንጅ አንደ አንተ የረከሰ አይደለም!!!

  4. I am really fed-up of this infantile so called journalist. Tesfaye has no right and caliber to advice Ethiopians. If he has a moral to talk, he should have told us about his fatherland dictator. Tadia tesfaye kebena kurt bamarew kuter ayenun Ethiopia lay yitelal. BUDA

  5. Shabia must know one basic fact, we gave you a life time lesson during the 1999-2000 war at Badme. I know you don’t forget how we fucked you. If you need more we are ready to fuck you again . We have been eating a lot of Mitmita and and Tere Sega. That is how we defeated your Italian masters. Tesfaye, the Shabia spy I believe you got the message.

  6. Tesfay is putting the reality from the beginning I dont understand why u guys are simply spread your senseless point if u have the gut and capable enough to defend his stand just do it, if not shut the f…up and learn ur false full story bzu yewesht tarik snsema ena snamn norenal ahun gn ybqa Ethio is not only Amhara there is no minilik The 1st ethio has only 130 years of history Jwahr Mohammod make it clear based on fact. stop saying 3000 yrs of bla bla your Minilk committed crime against our Oromo people Haileslase repeated again all your Amhara ethio history is based on full of fabrication yehn wehst yetmolabt ye amara tarik snsema norneal ahun lkachu sinegerachu menchachat………there is a doubt about battle of adwa and dogali as well how many of u know that the battle was between some 6000 italians and few eritreans mercenary or ‘banda’ but on your amhara ethio side more than 120 000 poor welayta oromo and …..other ethnics u amharas were talking all the time yehn tornet blachu stakabdu ena stagannu norachual. Tesfay telling u this……. your history is full of junk!!!!! he has nothing to do with shabya or eritrea……face the fact wake up!! at the expense of oromia u cant build ur amhara kingdom again, long live Oromia .

  7. Finfine above your a VERY big poop, “arre” go to a river and wash your body clean before you open your stinky mouth!

  8. Garoma………where shall I go and wash? all of our river land….. is evaded by neftegna tell your master to leave OUR place leave us alone hodam amara hula! tigre gud eyeserachu newe staweru………

  9. Finfine, if you have the guts and the commitment why don’t you fight us? Let me refresh your memory back in 1992 immediately after EPRDF removed the Derg regime, OLF’s 50,000 fighters were defeated by very few brave EPRDF forces. OLF is more than 40 years old but didn’t even control 40 cm of land. Finfine and friends should be grateful for EPRDF for liberating you from Amhara masters. If EPRDF don’t take care of you the Amharas will use you like donkeys.

    • ‘Fight us’ …ohhhhh u guys still think like primitives OLF don’t need to fight we are in the heart our people don’t u know each and every Oromo is in our side, we don’t need to control our people, u see the difference for u guys its all about land bullet fight …….u have to have your peoples will u have to live in the heart of ur people its not about Dedebit to Finfiné its not about expansion invading………its to have the peoples will u sound that u from the up shame on u leba tigré

  10. bravo tesfaye alamah tesakaleh enquan des aleh. ayehw aydel endet bante tshuf bekalat mebalat endejemeren. kelay yetetsafuten asteyayet setaneb westih yerekal. lante yehie yehiwot menged new. berta tinesh tesaktolehal bizu yikerhal. anyways do you really love oromo people ? i don’t think. do you love Ethiopian people ? i don’t think. do you love Eritrean people ? i don’t think. tesfaye so what do you love?????????????????????????????????????????????????????
    don’t say just writing this is not writing b/c every writing has its own purpose. it is known Ethiopia has never good government (since today) we heard many worst things done by government bodies just to keep their power. on the top of that your books are the worst than any thing. i think your mind setup and spirit comes from evil.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*