ለመሆኑ የከሰረው ማነው?

ዳዊት ከበደ

ሀገሬን ከለቀቅኩ ድፍን አንድ ወር ሞላኝ። በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳትታይ የተፈረደባት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣም ህትመቷ ከቆመ እነሆ አራት ቅዳሜዎች አለፉ። በሽመልስ ከማል የቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመራው አዲስ ዘመን ግን ስድቡን አላቆመም።