የሊዝ አዋጁ ከንግዱ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
– በስብሰባው የተጋበዙ የመንግሥት ባለሥልጣን ሳይገኙ ቀሩ
ባለፈው ዓርብ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው ሁለተኛው አዲስ ቻምበር ቢዝነስ ፎረም አጀንዳ ሆነው የቀረቡት የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አዲሱ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቢሆኑም፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በአዋጁ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አንስቷል፡፡