ዓቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ

•    540 ገጽ የሰነድ ማስረጃና 35 የሰው ምስክሮችን አቅርቧል

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ክስ ከመሠረተባቸው 24 ተጠርጣሪዎች መካከል፣ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን በሚከታተሉት ስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ ከታኅሣሥ 6 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ምስክሮቹን ማሰማት ጀመረ፡፡