ናይጀርያ መለስ ዜናዊ በኢትየጵያ የአልቃይዳ የወታደራዊ ስልጠና ማእከል እያቋቋመ ነው ስትል ከሰሰች ፣ ይህም የወያኔ አሸባሪነት በሚገባ አጋልጦ እርቃኑን ያስቀረ ነው ተባለለት!
ቦኮ ሀራም በመባል የሚታወቀውና በናይጄሪያ የሚንቀሳቀስ አንድ ኢስላማዊ ድርጅት በርካታ አባላት በፖሊስ ከተያዙ ቦኋላ ስለድርጅታቸው መረጃ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን የገለጸው የናይጄሪያ መንግሥት ብዙ ጊዜ ከፈጀ እልህ አስጨራሽ ምርመራ ቦኋላ የድርጅቱ አባላት ስልጠና የሚያገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ናይጀሪያ ይፋ አድርጋለች።
በቦካ ሀራም ስም ናይጀርያ ውስጥ የምንቀሳቀስው ይህ እስላማዊ ድርጅት ዋና አላማው በናይጀርያ የሸሪያ ህግ እነዲተገበር የሚታገል ሲሆን ከአልቃይዳ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝም በተለያዩ ጊዜያቶችም የሽብር ጥቃቶችን በመፈፀም የህይወትና የንብረት ጥፋት ማድረሱን የናይጀሪያ መንግሥት ይፋ ሲያደርግ ቆይቶአል።
ከናይጀሪያ ፖሊስ ምንጮች ተገኘ ተብሎ ይፋ የሆነው ዜና እንዳመለከተው፤ የድርጅቱ አባላት በናይጀሪያ ፖሊሶች ቁጥጥር ሥር ሆነው በተካሄደባቸው ምርመራ ምንም መረጃ ላለመስጠት ብዙ ሲያንገራግሩ ከቆዩ ቦኋላ የሚሰጡት መረጃ ይፋ እንዳይሆን ቃል በማስገባት በሰጡት ምስክርነት አባላቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጠና እንደሚሰጣቸው በማጋለጣቸው ናይጀርያ በሁኔታው እጅግ በመቆጣት ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ቅሬታዋን አቅርባለች።
ቦኮ ሀራም የተሰኘው የአልቃይዳ ቅርንጫፍ የሆነው የአሸባሪ ድርጅት በቋሚነት በሶማሌያና ሱዳን የማሰልጠኛ ማእከል ያሉት ሲሆን በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አዲስ የማሰልጠኛ ካምፕ መክፈቱን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ይሀው የአሸባሪው ተቋም ከመለስ ዜናዊ ጋር በመመሳጠር የአሸባሪዎች ማሰልጠኛ ካምፕ ሊያቋቁም የቻለው፣ ከምእራባዊያኑ አለም እየተከሰሰ በመጣው ጫና እነዲሁም፣ በቦኮ ሀራም እና አልቃይዳ መካከል ያለው የአላማ ትስስር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጭምር ከታወቀ በኃላ መሆኑ ብዙዎችን አስገርሞአል።
መለስ ዜናዊ በአሁኑ ወቅት ስልጣኔን ይቀናቀኑኛል ብሎ የሚፈራቸውን ሰላማዊ ዜጎችን በአሸባሪነት እየወነጀለ በተፈበረከ ማስረጃ ወሂኒ ውስጥ እያሰቃዬ እንደሚገኝ በምዕራባዊያን ወድጆቹ ጭምር እየታወቀ መጥቶአል።
በምስራቅ አፍሪካ አለመረጋጋትን ፈጥሮ ሰላም አስከባሪ መስሎ ለመታየት የሚያደርገው ሙከራ በም ዕራባዊያን ዘንድ ብዙም ትኩረት ስላላገኘ የአለመረጋጋት አድማስ ወደ ምዕራብ አፍሪካ በማስፋት በንጽፅር በአህጉሩ ደረጃ ካሉት አገሮች የተሻለ መሪ ሆኖ ለመታየት ሲል እንዲህ አይነት የሌላውን አገር ተቃዋሚ የማሰልጠንና የማደራጀት ተግባር ውስጥ እንደገባ አንዳንድ የፖለቲካ አዋቂዎች ይናገራሉ።
የናይጀሪያ ፖሊስ በሰጠው ተጨማሪ መግለጫ ፣እነኚሁ ሀይላት የሰለጠኑትን አባለቶቻቸውን መልሰው ወደናይጄርየ ለመላክ ነው ትልማቸው፣ይህም ከጥርጣሬ ነፃ ለመሆን ሰልጣኞቻቸውን መጀመርያ ወደአውሮፓ ልከው በአውሮፓ ፓስፖርት ወደናይጀርያ የሚገቡበትን ሁኔታ ነው እያመቻቹ ያሉት፣ ከዚህም ባሻገር ወደአውሮፓና ዱባይ ሲላኩ አለባበሳቸወን ከህብረተሰቡ ጋር በማመሳሰል ያለጥርጣሬ የስውር አላማቸውን ከግብ የሚያደርሱበት ሁኔታ እያመቻቹ እንዳሉ አሳውቋል።
የናይጀርያ ፖሊስ ጉዳዮች ሚንስቴር የሆኑት አየር ወለድ ካፒቴን ካሌብ ኦሉቦላድ፣ የናይጀሪያ የደህንነት ቢሮ አመርቂ የሚባል አቀራረብ እነዳልነበረና ይህ ክስተት ግን ቢሮው በቁሳቁስ ይበልጥ እነዲደራጅ ያነቃውና አዲስ አካሄዶችን በመቀየስ የሀገሪትዋን ደህንነት ለማስጠበቅ በርትተው እነዲሰሩ እንዳደረጋቸው ጨምረው ገልፀዋል።