ኢንጂነር ግዛቸው ከአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ራሳቸውን አገለሉ
– ዶ/ር ነጋሶ የአንድነት ሊቀመንበር ሆነው ዳግም ተመረጡ
ከስድስት ዓመታት በላይ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በመሳተፍና በፓርቲዎቹም ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ከአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ተመራጭነት ራሳቸውን አገለሉ፡፡