ፍኖት – ደቡብ ክልል በሚገኘው ደቡብ ኦሞ ዞን አንድ ስው ሲሞት 18 ሰዎች ታሰሩ
ገሊላ ወረዳ ሰሜን አሪ በሚባል ቦታ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ.ም በግብርና ሙያ ቨሚተዳደር አቶ ለጊዜ ወርቅማ
በፖሊሶች ተዘርፎ ጉዳት እንደደረሰበት ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል፡፡ አቶ ለጊዜ ወርቅማ ከማሳው ቡና ለቅሞ ወደ ቤቱ እየሄደ ሳለ ወረዳው በሚገኙ በመንግሥት ፖሊሶች ዝርፊያና ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ሕዳር 13 ቀን 2004 ዓ.ም ለሕክምና ዕርዳታ ሄዶ ሕይወቱ አልፏል፡፡
በአቶ ለጊዜ ወርቅማ ላይ ፖሊሶቹ ዝርፊያና ጉዳት ሲያደርሱ አይተናል ያሉ 18 ምስክሮችም በእስር ላይ እንደሚገኙና እነኚህም ሰዎች ከዚህ በፊት የቀድሞ የአንድነት ደጋፊ በመሆናቸውና አሁን ግን በተጐጂው ግለሰብ ዙሪያ ሊመሰክሩ ሲሄዱ እንደታሰሩ ተነግሯል፡፡
ከታሳሪዎችም መካከል አቶ አብሪ አየለ፣ካሱ ገመዳ፣ አየለ ባቢላሮ፣ከበደ ወርቅማ፣ዋጃ ዳውካ፣ወ/ሮ ዘነበች ፎርጫና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡ ይህንንም ለማጣራት ወደ ወረዳው አስተዳደር ኃላፊ ወደ ሆኑት አቶ ታፈሰ ጋ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው
የአንድነት ፓርቲ ለሕዝብ መብት መከበር የቆመ፣ በአገር ዉስጥ በሰላም የሚታገል ፣ በአገር ቤት ኢትዮጵያዉያንን ለማደራጀት የሚንቀስቀስ የሰለጠነ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት ነዉ። ሕዝቡን ለማስተማርና ለማንቃትም በየሳምንቱ የፍኖት ጋዜጣን አትሞ ያስራጫል። የፍኖት ጋዜጣን በብዛት ለማሳተምና በስፋት በየክልሎቹ ለማሰራጨት ከፍተኛ የገንዝብ አቅም ይጠይቃል። በአገር ቤት ከሚታገሉ ወገኖቻችን ጎን ይቁሙ ! በገንዘብዎት የአንድነት ፓርቲን ይደግፉ !