አንድነት ከብርሃን ፓርቲ ጋር ተዋሀደ

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር ተዋሀደ ።

የሁለቱ ፓርቲዎች ውህድ የሆነውን አዲሱን አንድነት ለፍትህ እና ለዲምራሲ ፓርቲ እንዲመሩም ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በሊቀ መንበርነት መርጧል ። ፓርቲውን በበላይነት የሚመሩ 55 የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ምርጫም አካሂዷል ። ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ራድዪ ና ቴሌቭዥን አኬልዳማ በሚል ርዕስ ለህዝብ የሚቀርበው ፕሮግራም ፓርቲውን ከህዝብ ለመነጠል የታቀደ ነው ሲል ቅሬታውን ገልፃል ።

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ዘገባን ያድምጡ
[podcast]http://radio-download.dw.de/Events/dwelle/dira/mp3/amh/EFD410B4_2.mp3[/podcast]