ህወሓትና ፒራና

ግርማ በላይ

በትግርኛ ”ጠዓመኒ ድግመኒ” የሚባል አነጋገር እንዳለ አውቃለሁ። በአማርኛም ”ጣመኝ ድገመኝ” የሚል አይኖርም ብዬ አላስብም። ባለፈው ከኢትዮሚዲያ የአንድ ሰው ጽሑፍ ተነስቼ ስለወያኔ ዛፍ የሞነጫጨርኩዋት ወረቀት በሰደድኩዋት አብዛኛው ቦታ ስላየሁዋት ብርታት ሰጠችኝና አሁንም ኪቦርዴን አነሳሁ – ’ብዕር’ እየቀረ አይደል?! ስንት ዘመን ለፍቶ ሲያበቃ ኪስ ማሞቂያ ሆኖ መቅረቱ ግን ትንሽ ቅር ማሰኘቱ አይቀርም።