የብአዴንን ልደት ለማክበር በአዲስ አበባ የተጠራው የጽዳት ዘመቻ በተሳትፎ እጥረት ከሸፈ
ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ – ብአዴን – የተባለው የወያኔ ተለጣፊ ፓርቲ የልደት ቀኑን ለማክበር በአዲስ አበባ የጠራው የጽዳት ዘመቻ የከተማውን ህዝብ ቀልብ ለመሳብ ባለመቻሉ ሳይሳካ መቅረቱን ከመዲናይቱ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።
ላለፉት ሃያ አመታት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ረግጦ እንዲገዛ ሲያቀናጅ የቆየው እና እንደበረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ እና ተፈራ ዋልዋ ባሉ በህዝብ የተጠሉ ግለሰቦች የሚመራው ድርጅት እወክለዋለሁ በሚለው የአማራ ህዝብ ዘንድ በንቀት እንደሚታይ ይታወቃል።
ብአዴን በአዲስ አበባ በጠራው የጽዳት ዘመቻ ላይ አሳፋሪ የሆነ የሰው ቁጥር መገኘቱ፣ የወያኔ አገዛዝ እና ተለጣፊ ድርጅቶቹ ለመልካም አላማ እንኳ ህዝብ ማሰባሰብ እንዳቃታቸው ጉልህ ማስረጃ ነው ሲሉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።