የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ሀገር ወዳድና … ኢህአዴግ ከዚህ ወዴት? ክ.12 (አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ ሁለት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ፣፬፦ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድሕ)፣ ፓሪስ ሁለት ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው ደርግ ሲወገድ የህዝባችን ምኞትና ጥባቆ ለዝንታለም ቀስፈው የያዙት የአመረባገነን ስርአቶች አዙሪት እንዲያከትምና መሰረታዊ የሆኑና ስር የሰደዱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የወል ችግሮቻችን በሰከነ ሀገራዊ የእርቅና ሰላም ሂደት የሚፈቱበት መንገድ ይመቻች ይሆናል የሚል ነበር።