በህገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የሚወጣ ገንዘብና ተፅዕኖው
እ.ጎ.አ በ 2009 ብቻ ከኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ ወደ 3.26 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ አንድ ዓለም ዓቀፍ ተቋም አስታወቀ። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንግሪቲ የተባለው ድርጅት ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው ገንዘቡ ከዚያ በቀደሙት 2 ዓመታት ከሃገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ ከወጣው ገንዘብ በእጥፍ ይበልጣል ። ተቋሙ ባወጣው ጥናታዊ ፅሁፍ ይኽው ገንዘብ በሙስና በጥቅማ ጥቅምና በስርቆት ከሃገር እንደሸሸ ጠቁሟል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል። ያዳምጡ