ጌቱ ገለቴ በተከሰሱበት ወንጀል በ10 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ
– ጉዳያቸው በሚዲያ እንዳይዘገብ ተጠየቀ
(በኃይሌ ሙሉ)
ወይዘሪት ሄለን አንበሴ ግሩም በተባሉ ግለሰብ ላይ የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በዓቃቤ ሕግ የተከሰሱት የጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና የጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር ባለቤት አቶ ጌቱ ገለቴ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ከትናንት በስቲያ ቀርበው በ10 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ፡፡