ፍኖት- አንድነትን ለሚቀጥሉት ዓመታት ፓርቲውን የሚመሩ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እየቀረቡ ነዉ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ቅዳሜ ሕዳር 30 እና እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም 2ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡ ፡
በጠቅላላ ጉባዔውም አባላት፤አንድነት ፓርቲ ከብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር ያደረጉትን ውህደት እና ከመድረክ አባላት ፓርቲዎች ጋር የተፈጠረውን ግንባር እንደሚያፀድቁት ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ለሚቀጥሉት ዓመታት የብሔራዊ ም/ቤት አባል በመሆን የሚያገለግሉ አባላትን እንደሚያስመርጥ ተጠቁሟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲውን ለሚቀጥሉት ዓመታት በሊቀመንበርነት የሚመሩ ዕጩዎች በተወዳዳሪነት ራሳቸውን እንዲያቀርቡና ቋሚ አባላትም ጥቆማ ማድረግ እንደሚችሉ መገለጹ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት በሚቀጥሉት ዓመታት ፓርቲውን ለመምራት በዕጩነት የቀረቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ዶ/ር ንጋት አስፋው እና ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ መሆናቸውን የጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ አባል አቶ ፀጋዬ አላምረው ለዝግጅት ክፍላችን ገለፀዋል፡፡
በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረትም በጠቅላላ ጉባዔው የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው የሚመረጡት ወደፊት በተሻለ ደረጃ የሕዝቡንና የፓርቲውን ዓላማ ለማሳካት ይሰራሉ የተባሉ ሌሎች አመራሮችን የመምረጥና በጋራ የመሥራት ሥልጣን እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ ጠቅላላ ጉባዔውም የሚካሄደው ሜክሲኮ በሚገኘው ዲ-አፍሪክ ሆቴል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ለሕዝብ መብት መከበር የቆመ፣ በአገር ዉስጥ በሰላም የሚታገል ፣ በአገር ቤት ኢትዮጵያዉያንን ለማደራጀት የሚንቀስቀስ የሰለጠነ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት ነዉ። ሕዝቡን ለማስተማርና ለማንቃትም በየሳምንቱ የፍኖት ጋዜጣን አትሞ ያስራጫል። የፍኖት ጋዜጣን በብዛት ለማሳተምና በስፋት በየክልሎቹ ለማሰራጨት ከፍተኛ የገንዝብ አቅም ይጠይቃል። በአገር ቤት ከሚታገሉ ወገኖቻችን ጎን ይቁሙ ! በገንዘብዎት የአንድነት ፓርቲን ይደግፉ !
ፍኖት እትም 19ን በሙሉ ለማንበብ ከዚህ ይጫኑ !