አቶ ብሩንም ገደሉት (ነፃነት ዘገዬ)

ነፃነት ዘገዬ

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ዶ/ር እሌኒ ስለምትባል ወጣት ኢትዮጵያዊ ምሁር ሲያቀብጠኝ በእንግሊዝ አፍ ጽፌ በላክሁት ጦማር ሳቢያ በደረሰብኝ የሞራል ውድቀት ላለፉት ብዙ ጊዜያት አንገቴን ደፍቼ ምንም ሳልል ቆይቻለሁ። አሁን ግን ”እስከመቼ ኩርፊያ?” ብዬ ተደፋፈርኩና ብዕሬን አነሳሁ። የሚገርመው የት ጠፋ ብሎ አንድም ሰው አልጠየቀኝም። እንዴህ ነን እንዴ ለካ? ትዝብት ነው ትርፉ!