… ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? (ክ.11 – አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አንድ
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
ሐ) አመራር፦ ቀደም ሲል እንዳየነውና ወደፊትም እንደምንመለከተው ለማንኛውም የተናጠልም ሆነ የጋራ ትግል መሳካት ወይም ውድቀት አመራር ቁልፍ የሆነ ሚና አለው። በመሠረቱ የትግል ድርጅት አመራር ሰጭ መሆን ከፍተኛ ኃላፊነት ስለሆነ በኅሊና ተገዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት እንጂ የግል ጥቅም የሚገኝበትም ሆነ አጉል ዝና የሚፈለግበት ሹመት ተደርጎ መታዬት አይኖርበትም።