የአዲሱ የኔቶ ዋና ጸሐፊ ኃላፊነቶችና ተግዳሮቶች

ሚስተር የንስ ስቶልቴንበርግ 28 አባል መንግሥታት የሚገኙበትን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶ አዲስ ዋና ጸሐፊ ሆነው ስራቸውን በይፋ የጀመሩት ባለፈው ረቡዕ ነበር። ስቶልቴንበርግ ግዙፉ የምዕራባዉያን ወታደራዊ ግንባር ከዚህ ቀደም በበላይነት የመሩት አንደርስ ፎኽ ራስሙሰንን ነው የተኩት።